(310) 649-5030 res@selamtravel.com

ISRAEL - THE HOLY LAND

JERUSALEM, BETHLEHEM, JERICHO, NAZARETH, AND MANY MORE

ISRAEL THE HOLY LAND

JERUSALEM, BETHLEHEM, JERICHO, NAZARETH, AND MANY MORE

Celebrate Easter in the Holy Land

Holy Land Easter Itinerary

9

ቀን ፩

ምዕመናን እንግዶች እሥራኤል በን ጎርዮን አየር ማረፊያ እንደደረሱ የፕሮግራሙ አዘጋጅና የኤጀንሲው ባልደረቦች ይቀበሉዋቸዋል፡ ፡ እንግዶቹ በአንድነት ወደ ኢየሩሳለም በአውቶቡስ ይጉዋዙና በተዘጋጀላቸው ሆቴል የየክፍላቸውን ቁልፍ ይቀበላሉ። በዚያው (የፆም)እራት ተመግበው አዳር ያደርጋሉ።

9

ቀን ፪

ወደ ኢየሩሳሌም አሮጌው ከተማ ጉዞ ያደርጉና ጉብኝት ይጀምራሉ፤ በአጸደ ሐምል- ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጸለየበትን፤ በጌቴሴማኒ- እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተቀበረችበትንና በክብር የተነሳችበትን ፍልሰታ ለማርያም በቅደም ተከተል ይጎበኛሉ። ቤተ-ሳይዳ- የ38 ዓመታት ሕመምተኛው መጻጉዕ የተፈወሰበት ሥፍራና ይሁዳ የተቀበለውን ብር መልሶ እራሱን ሰቅሎ የሞተባትን (ዛፍ) ይመለከታሉ፡፡ ከዚያ ወደ ጲላጦስ አደባባይ የእግር ጉዞ ያደርጉና ክቡር መስቀሉን ተሸክሞ በፍኖተ መስቀል ጎዳና በሚደረገው ጉዞ ላይ ተካፋይ በመሆን ከምዕራፍ አንድ እስከ ምዕራፍ አሥራ አራት በጌታ ኢየሱስ ላይ የተፈጸመውን ሕማመ መስቀሉን እያሰቡ እስከ ዴር ሡልጣን የኢትዮጵያ ገዳም ድረስ ይጓዛሉ፤ ቀጥሎም በዴር ሡልጣን የኢትዮጵያ ገዳም ውስጥ የበዓለ ስቅለቱን ጸሎት፤ ግብረ ሕማማቱን በመስማት ስግደት በመስገድ ይውላሉ፡፡ ጥብጠባ ተደርጎ ከበዓሉ ዑደት ፍጻሜ በኋላ ወደ ሆቴል በመመለስ የፆም እራት ተመግበው አዳር ይሆናል፡፡

9

ቀን ፫

ወደ ኢየሩሳሌም አሮጌው ከተማ ጉዞ ያደርጉና ጉብኝት ይጀምራሉ፤ በአጸደ ሐምል- ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጸለየበትን፤ በጌቴሴማኒ- እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተቀበረችበትንና በክብር የተነሳችበትን ፍልሰታ ለማርያም በቅደም ተከተል ይጎበኛሉ። ቤተ-ሳይዳ- የ38 ዓመታት ሕመምተኛው መጻጉዕ የተፈወሰበት ሥፍራና ይሁዳ የተቀበለውን ብር መልሶ እራሱን ሰቅሎ የሞተባትን (ዛፍ) ይመለከታሉ፡፡ ከዚያ ወደ ጲላጦስ አደባባይ የእግር ጉዞ ያደርጉና ክቡር መስቀሉን ተሸክሞ በፍኖተ መስቀል ጎዳና በሚደረገው ጉዞ ላይ ተካፋይ በመሆን ከምዕራፍ አንድ እስከ ምዕራፍ አሥራ አራት በጌታ ኢየሱስ ላይ የተፈጸመውን ሕማመ መስቀሉን እያሰቡ እስከ ዴር ሡልጣን የኢትዮጵያ ገዳም ድረስ ይጓዛሉ፤ ቀጥሎም በዴር ሡልጣን የኢትዮጵያ ገዳም ውስጥ የበዓለ ስቅለቱን ጸሎት፤ ግብረ ሕማማቱን በመስማት ስግደት በመስገድ ይውላሉ፡፡ ጥብጠባ ተደርጎ ከበዓሉ ዑደት ፍጻሜ በኋላ ወደ ሆቴል በመመለስ የፆም እራት ተመግበው አዳር ይሆናል፡፡

9

ቀን ፬

ጠዋት በአስራ ሁለት ሰዓት (06፡00) ላይ ወደ አሮጌው ከተማ ጉዞ ያደርጉና ከዴርሡልጣን ገዳም አውደ ምሕረት ይደርሳሉ፡፡ ከዚያም የቅዳም ሥዑር (ቄጠማ)በዓል ሥርዓተ ጸሎት ላይ ተካፋይ በመሆን በረከት ይቀበላሉ፡፡ የበዓሉ ሥነ ሥርዓት እንደተፈጸመ ወደ ቤተልሔም ከተማ ጉዞ ያደርጋሉ፡፡ በቤተ ልሔም ከተማ፤ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደባትና እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ያጠባችበት የወተቱ ዋሻ የተባለው (Milk Groto) ቅዱስ ሥፍራዎች፤ የኢትዮጵያ ደብረ ሰላም ኢየሱስ ገዳም፤ የእረኞቹ መንደር (The Shepherds Fields) በቅደም ተከተል ይጎበኛሉ፡፡ በቤተ ልሔም አካባቢ ምሳ ይመገቡና ወደ ኢየሩሳሌም ይመለሳሉ፡፡ ለትንሳኤው ክብረ በዓል መላው ምዕመናን በኢትዮጵያ የሀገር ባህል ልብስ፤ ቤተ ክርስቲያን ጉዞ ያደርጋሉ፡፡ የሌሊቱን ቅዳሴ አስቀድሰው በረከት ይቀበላሉ፡፡ የሌሊት መግደፊያ እራት በዚያው ከተቋደሱ በኋላ ወደ ሆቴል ይመለሳሉ፡፡
9

ቀን ፭

ስለ በዓሉ ክብር የግማሽ ቀን እረፍት ያደርጋሉ። የፍስክ ምሳ በሆቴል ይመገባሉ። ከምሳ በኋላ ወደ ጎልጎታ ቤተ ክርስቲያን በማምራት በውስጡ የሚገኙትን ቅዱሳት መካናት በቅድመ ተከተል እየጎበጙ ይሳለማሉ። ከዚያ ወደ ሆቴል በመመለስ የፍስክ እራት ተመግበዉ አዳር ይሆናል።

9

ቀን ፮

ጡዋት በአሥራ ሁለት ስዓት (6፡00) ላይ ወደ አዲሱ ከተማ ጉዞ ያደርጉና በደብረ ገነት ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ያስቀድሳሉ። ቅዳሴው ሲፈጸም ወደ ሆቴል ተመልስው ቁርስ ከተመገቡ በኋላ ወደ ደብረ ዘይት ተራራ በመጉዋዝ በአካባቢው የሚገጙትን ቅዱሳት መካናት፦ ቤተ ፋጌ-መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሆሣዕናውን ጉዞ የጀመረበት፣ እርገት-ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክብር ያረገበትና አቡነ ዘበሰማያት ያስተማረበት ያድርበት የነበረው የኤሌዋን ዋሻ ይጎበኛል።

9

ቀን ፯

በኢያሪኮ መሥመር በዮርዳኖስ ሸለቆ በአውቶቡስ ወደ ጥብርያዶስ ከተማ (120 ኪሜ) ርቀት ይጓዛሉ። በኤያርኮ ከተማ ውስጥ፤ በገዳመ ቆረንቶስ- ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ 40 ሌሊት 40 ቀን የጸለየባትን ይጎበኛሉ። በነቢዩ ኤልሳ ስም ከሚጠራው መንፈሳዊ ታሪክ ካለው ምንጭ ጸበል ይጠጣሉ። በዘኬዎስ ስም የሚጠራው ዋርካ ዛፍ፣ የኢትዮጵያ ቤተ ገብርኤል ገዳም በቅድመ ተከተል ይጎበኛል፡ በቆሮንቶስ ተራራ ሥር ምሳ ይመገቡና አዳር ናዝሬት ከተማ ሆቴል ይሆናል።
9

ቀን ፰

በገሊላ ባህር ዙሪያ የሚገጙትን ቅዱሳት መካናት ለመጎብኘት ይንቀሳቀሳሉ፡ ቅፍርናሆም፣ ጥንታዊው የአየሁድ ምክራብ፣ የቤተ ሳይዳ መንደር ፍርስራሽአንቀጸ ብፁዓን፣ የተራራው ስብከት ያስተማረበት(የሓዋርያው ማቴዎስ ቤት)በሁለት ዳቦ፣ በአምስት ዓሣ አበርክቶ 5000 ሺህ ሕዝብ የመገበበትና የቅዱስ ጴጥሮስ ቤር ክርስቲያን በቅድም ተከተል ይጎበኛሉ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀበት ቦታ ዮርዳኖስ ይጠመቃሉ። በገሊላ (ጥብርያዶስ) ባሕር በታንኳ ተሳፍረው በባሕሩ ላይ ትምህርት እየተሰጠ ጉዞ ያደርጋሉ። ወደ ሆቴል በመመለስ እራት ተመግበው አዳር ያደርጋሉ። ናዝሬት ከተማ

9

ቀን ፱

ወደ ናዝሬት ከተማና ወደ ቃና ዘገሊላ መንደር በመጓዝ በዚያ የሚገኙትን ቅድሳት መካናት በቀደም ተከተል በመዘዋወር ይጎበኛሉ፣ ይሳለማሉ። እንደዚሁም፣ ደብረ ታቦር፣- ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ባህርያ መለኮቱን የገለጸበት፣ ቃና ዘገሊላ፣- ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ በሠርጉ ቤት ተገኝቶ ውሃውን ወደ ወይነ ቃና በመለወጥ የመጀመሪያውን ታምራት ያደረገበት፣ ናዝሬት፣- እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ብሥራት የተቀበለችበትን ከምንጭ ውሃ ትቀዳበት የነበረበረውንና ቤተ ዮሴፍ የተባለውን ቅዱስ ሥፍራ፣ በላያቸው ላየ የታነጹትን ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት ይጎበኛሉ።

9

ቀን ፲

ከጥብርያዶስ ወደ ቴል አቪቭ ከተማ ረጅም ጉዞ ያደርጋሉ። እግረ መንገዳቸውን ግራ ቀኙን የእስራኤል አገር ልማት የገበሬዎች የእርሻ ጣቢያ እየተመለከቱ ወደ ሓይፋ ከተማ ያመራሉ፤ በዚያ በቀርሜሎስ ተራራ ላይ የሚገኘውን የነቢዩ ኤልያስን ቤተ ክርስቲያን ይጎበኛሉ።

9

ቀን ፲፫

በዓይነ ከርም መንደር የዘካርያስና የኤልሳቤጥ መኖርያ የነበሩትን ቤተ መቅደሶች ይጎበኛሉ ፤ የእረፍት ቀን ይሆናል። በሆቴል እራት ተመግበው አዳር ይሆናል።

9

ቀን ፲፪

ወደ እየሩሳሌም በመጓዝ የዳግሚያ ትንሳኤን በዓል በደብረ ገነት ኪዳነ ምሀረት ቤተ ክርስቲያን ወይም በዴር ሡልጣን መድኃኔ ዓለም ገዳም ቅዳሴ አስቀድሰው በዓሉን ያከብራሉ፤ በመቀጠል በዓይነ ከርም መንደር የዘካርያስና የኤልሳቤጥ መኖርያ የነበሩትን ቤተ መቅደሶች ይጎበኛሉ፤ በሆቴል እራት ተመግበው አዳር ይሆናል።

9

ቀን ፲፬

መንገደኞቹ እንደ በረራ ሰዓታቸው ወደ አየር መንገድ ይጓዛሉ፤ በዚህ የመጨረሻው ስንብት ይሆናል። ኢትዮጵያውያን ምዕመናን በኢየሩሳሌም የቅዱሳት መካናት መንፈሳዊ
ጉብኝት ለማድረግ ዕድል እንዲገጥማቸው ከልብ እንመኛለን፤ ፍፃሜውን እግዚአብሔር ያሳምረው።

GALLERY